ወደ ራዳር የመንጃ ፍቃድ ትምህርት ቤት እንኳን በደህና መጡ

ዋጋችን ከደንበኞቻችን አቅም ጋር የተመጣጠነ ሲሆን ሰልጣኞቻችን በሚችሉት አቅም አንድ ጊዜ ፣ሁለት ግዜ ወይም ሶስት ግዜ እንዲከፍሉ አመቻችተናል።

የሞተርሳይክል ስልጠና

አውቶሞቲቭ ስልጠና

የህዝብ-1 ስልጠና

በአገራችን አብዛኛው የትራፊክ አደጋ በአሽከርካሪዎች ችግር የሚደርስ ሲሆን ይህንን አሳሳቢ ችግር ለመቅረፍ በትራንስፖርት ኢንደስትሪው ዘርፍ በአሽከርካሪዎች ብቃት፣ በመሠረታዊ ቴክኒኮች እና በመንገድ ደህንነት ትምህርት የተማሩ አሽከርካሪዎች በቂ ስልጠና መስጠት ያስፈልጋል። የብዙ ግለሰቦችን ህይወት ለመታደግ ተገቢውን ትምህርት እና ስልጠና መስጠት አስፈላጊ ሲሆን ህይወትን ማዳን እና በግለሰብ፣ በቤተሰብ እና በንብረት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ መከላከል ያስችላል።

የራዳር መንጃ ፍቃድ ት/ቤት የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ብቁ አሽከርካሪዎችን በማፍራት ላለፉት አስራ አንድ አመታት በሺዎች የሚቆጠሩ በሥነ ምግባር የታነፁ፣ታማኝ እና ብቁ አሽከርካሪዎችን በማሰልጠን ላይ ያለ ኃላፊነት የሚሰማው ተቋም ነው። በቀጣይ ድርጅታችን የስልጠና ዘርፎችን በማስፋፋትና ቀልጣፋ አሽከርካሪዎችን በማፍራት የበርካታ ሰዎችን ከትራፊክ አደጋ በመታደግ በትኩረት እየሰራ ይገኛል።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ አዋጅ ቁጥር 1074/2010 መሰረት ብቁ አሽከርካሪዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚጠበቅባቸውን የአሽከርካሪነት ብቃት እንዲያሟሉ እያሰለጠንን ነው።

የራዳር መንጃ ፍቃድ ትምህርት ቤት ሰልጣኞችን ከመንዳት ክህሎታቸው በፊት ለግል ባህሪያቸው በማስቀደም መጥፎ ባህሪ ያላቸውን ሰልጣኞች በመለየት እና የሰልጣኝ አሽከርካሪዎችን ባህሪ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በማጥናት በአሽከርካሪ ባህሪ ላይ ሳይንሳዊ ስልጠና ይሰጣል።

ስልጠና የምንሰጥባቸው ዘርፎች (አገልግሎታችን)

የሞተርሳይክል ስልጠና

አውቶሞቲቭ ስልጠና

የህዝብ-1 ስልጠና

ደረቅ-1 ስልጠና

የህዝብ-2 ስልጠና

ደረቅ-2 ስልጠና

ምን የተለየ ያደርገናል?

  1. ሰልጣኞቻችን መደበኛ ስልጠና ከመጀመራቸው በፊት ስነ ምግባርን፣ የተሸከርካሪ ቁጥጥር እና የመንገድ ምልክቶችን ጨምሮ ሰፊ ስልጠናዎችን እንሰጣለን።
  2. ዋጋችን ከደንበኞቻችን አቅም ጋር የተመጣጠነ ሲሆን ሰልጣኞቻችን በሚችሉት አቅም አንድ ጊዜ ፣ሁለት ግዜ ወይም ሶስት ግዜ እንዲከፍሉ አመቻችተናል።
  3. የኛ ማሰልጠኛ መሥሪያ ቤት ቤተ መጻሕፍት፣ አውደ ጥናት እና የኮምፒውተር ክፍል ስላለው የበለጠ ተፈላጊ ያደርገዋል።
  4. የማሰልጠኛ ተቋማችን በጠንካራ የአመራር ቡድን የሚመራ ሲሆን ብቁ መምህራንና ቴክኒሻኖች አሉት።
  5. የክፍል ውስጥ ስልጠና መከታተል ግዴታ ሲሆን በተለያየ ምክንያት ለማይመቻቸው   ሰልጣኞች ሰኣት እያማቻቸን እንዲከታተሉ እናደርጋለን።  
  6. ሰልጣኞቻችን የተግባር ልምምዳቸውን አጠናቀው የመንገድ ትራንስፖርት የመጨረሻ ፈተና ከመሰጠታቸው በፊት በራሳችን መምህራን እና ገምጋሚዎች እንፈትናለን።